በሰሜን አሜሪካ በቤይ ኤሪያ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች እንደ ሁለተኛ ቤታቸው የሚቆጥሩት የቤይ ኤሊያ ሙስሊም ኢትዮጵያን ማህበር (EBAMA) ሴንተር የናንተን የልበቀና ቤተሰቦቹን ድጋፍ እየጠበቀ ይገኛል።
ላለፉት 22 ዓመታት የእውቀት እና የተርቢያ ማዕከል በመሆን ሲያገለግል የነበረውና በአነስተኛ ሊዝ በኪራይ ይጠቀምበት የነበር የኢባማ ማእከል በድንገተኛ የእሳት ቃጠሎ በመውደሙ ምክንያት የአካባቢው ሙስሊም ማህበረሰብ መሰብሰቢያ እና ለልጆቹ ቁርኣን መቅሪያ ማእከሉን አጥቷል።
በደረሰብን ሙሲባ አላህ እንዲክሰን እንማጸነዋልን።
በአዲስ መንፈስ ይህን ማእከል መልሰን ለማቋቋም በማሰብ የናንተን የወንድሞቻችንን ድጋፍ በመጠይቅ ላይ እንገኛለን።
ይህን የበርካቶች ተስፋ የሆነውን ማዕከል ወደቀድሞ አግልግሎቱ ለመመለስ ያቀደ ዓለም ዓቀፍ የድጋፍ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ለማከናወን በጣት ተሚቆጠሩ ቀናት ቀርተውታል።
በዚህ የሁለት ዓለም ቤታችሁን በምትገነቡበት ልዩ የድጋፍ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ላይ ሁላችሁም አሻራችሁን ታሳርፉ ዘንድ ኢባማ ጥሪውን ያስተላልፋል።
ተወዳጁ ነብይ (ሰ.ዓ.ወ) እንዳሉት “የሙስሊሞች አምሳያ በመዋደዳቸው፣ በመተዛዘናቸውና በመደጋገፋቸው፣ እንደ አንድ አካል ናቸው። አንዱ የአካል ሲሰቃይ መላ ሰውነት በእንቅልፍ ማጣት እና በትኩሳት ምላሽ ይሰጣል!”
ኢባማን ለመደገፍ ከታች ያሉትን አማራጮች ይጠቀሙ!
- PayPal: Ethiopian Bay Area Muslims Association, Inc
- Zelle: ebamafinance@gmail.com
- Venmo: @ebama2024
- GoFundMe: https://www.gofundme.com/f/rebuild-our-community-help-ebama-secure-community-center?attribution_id=sl:09b0869b-c248-40d5-b913-ae9971d15e5e&lang=en_US&utm_campaign=man_sharesheet_dash&utm_content=amp10_t1-amp13_t1-amp14_t2&utm_medium=customer&utm_source=copy_link
“በህብረታችን የማናልፈው ፈተና የማነሻገረው ድልድይ አይኖርም!”
የቤይ ኤሪያ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ማህበር (EBAMA)